
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ኅብረት ፓርላማ የ2015/16 የሥራ ዘመን መጠናቀቁን ተክትሎ ለ2017/18 ለሁለት ዓመታት የሚያገለግሉ አዲስ የተማሪዎች ኅብረት ፓርላማ ሥራ አስፈፃሚ አባላት ምርጫ ሰኔ 18/2016 ዓ.ም ተጠናቋል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ኅብረት ፓርላማ የሥራ አስፈፃሚዎች ምርጫ ተጠናቀቀ

- Details
አቶ አሰፋ ጨጉልኤ ከአባታቸው ከአቶ ጨጉልኤ ቂዳ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ሳባሬ ሳቂሞ በቀድሞ ጋሞ ጎፋ ክፍለ ሀገር በቦንኬ ወረዳ በገረሴ ከተማ በ1966 ዓ/ም ተወለዱ፡፡

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒቲ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 12ኛ ክፍል ተማሪ የአብሥራ ፍፁምና ዳግም ሰለሞን የጋሞ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ከሰኔ 10 – 15/2016 ዓ/ም ባዘጋጀው ዞናዊ የሳይንስና ፈጠራ ሥራዎች ኤግዚቢሽን ላይ የፈጠራ ሥራዎችን በማቅረብ ላደረጉት የላቀ ተሳትፎ ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲና ኮሚዩኒቲ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዕውቅናና የተሳትፎ ምስክር ወረቀት ተሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒቲ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በዞናዊ የሳይንስና ፈጠራ ሥራዎች ኤግዚቢሽን ላይ ተሳተፉ

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሥነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ተመራቂ ተማሪዎች ተመርቀው በሚሄዱበት የተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገጥሟቸውን አዲስ የሥራ አካባቢዎችና የሚሰጣቸውን ኃላፊነት በጥንቃቄ በመቀበል የሚሰጧቸውን ማኅበራዊ አገልግሎቶች ሥነ ምግባራዊ እንዲያደርጉ በሥራ ሥነ ምግባር መርሆዎች እና በሙስና ወንጀል ሕጎች ዙሪያ ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና አዘጋጅቷል፡፡ ስለሆነም ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ ከዚህ በታች በተያዘላችሁ ፕሮግራም መሠረት ሥልጠናውን እንድትካፈሉ እናሳስባለን፡፡

- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማኅበራዊ ሳይንስና ሥነሰብ ኮሌጅ በ«Geography and Environmental Studies» ትምህርት ክፍል በ«Environment and Natural Resource Management» ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ተማሪ ዕጩ ዶ/ር ዘውዴ ዓለማየሁ ሰኔ 21/2016 ዓ/ም ከጠዋቱ ከ2፡30 ጀምሮ የ3ኛ ዲግሪ ማጠናቀቂያ ምርምር ሥራውን የውጪና የውስጥ ገምጋሚዎችና አማካሪዎች በተገኙበት በዋናው ግቢ በድኅረ ምረቃ አዳራሽ ያቀርባል፡፡ ዕጩ ዶ/ር ዘውዴ ዓለማየሁ “LAND USE/LAND COVER CHANGE AND CLIMATE CHANGE: EFFECTS ON HYDROLOGICAL PROCESSES IN GILGEL GIBE CATCHMENT, ETHIOPIA” በሚል ርዕስ የመመረቂያ ጥናት ጽሁፍ አከናውኗል፡፡