
- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሥር የሚገኘው ‹‹የአርባ ምንጭ የሥነ ሕዝብና የጤና ምርምር ማእከል›› በአርባ ምንጭ ከተማ የሚከናወን የሥነ ሕዝብ እና ጤና ጥናት ሥርዓት/Urban Health and Demographic Surveillance System/ ይፋ አድርጓል፡፡ ማእከሉ በአርባ ምንጭ ከተማ ላይ በተመረጡ ሰባት ቀበሌያት ለሚያደርገው ጥናትም ለመረጃ ሰብሳቢዎች፣ ለመረጃ ሰብሳቢ ተቆጣጣሪዎችና ለመረጃ አስተዳደር ሠራተኞች ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

- Details
በማኅበራዊ ሳይንስና ሥነ ሰብ ኮሌጅ የጂኦግራፊና አካባቢ ጥናት ት/ክፍል ከጋሞ ዞን ከተማና ፕላን መምሪያ ጋር በመተባበር ከጥር 5-8/2017 ዓ/ም ለዞን፣ ለወረዳና ለከተማ አስተዳደር ስታትስቲክስ ባለሙያዎች በ‹‹GIS›› ምንነትና አጠቃቀም ላይ በኮሌጁ የGIS ማዕከል ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ከሳውላ ካምፓስ ኃላፊ ጋር በ2017 ዓ.ም ተግባራዊ የሚደረግ የቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም ውል (KPI) ተፈራርመዋል፡፡
Read more: የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ከሳውላ ካምፓስ ኃላፊ ጋር የቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም ውል (KPI) ተፈራረሙ

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ጽ/ቤት በሥሩ የሚገኙ የሥራ ክፍሎችን የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን ገምግሟል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: የፕሬዝደንት ጽ/ቤት በሥሩ የሚገኙ የሥራ ክፍሎችን የግማሽ ዓመት የሥራ ሪፖርት ገመገመ

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በሥሩ ከሚገኙ የሥራና የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች ጋር በ2017 ዓ.ም የሚተገበር የቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም ውል (KPI) ጥር 7/2017 ዓ.ም ተፈራርሟል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በሥሩ ከሚገኙ የሥራና የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች ጋር የቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም ውል (KPI) ተፈራረመ