
- Details
Arba Minch University along with Centre International de Mathématiques Pures et Appliquées, CIMPA, Pharmaceutical Information Management System, PIMS, International Centre for Mathematical Sciences, ICMS, and European Mathematical Society, EMS, hosted an international collaborative Workshop on Bioinformatics and Mathematical Modeling of Infectious Diseases from December 18th to 22nd, 2023. Click here to see more photos.
- Details
የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ከትምህርት ሚኒስቴርና ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ከወልቂጤ፣ ወራቤ፣ ዋቸሞ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ጂንካ እና አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲዎች ለመጡ የግዥና ንብረት እንዲሁም የፋይናንስና በጀት አስተዳደር ኃላፊዎች፣ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች፣ የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና መከታተያ ክፍል ሥራ አስፈጻሚዎች፣ የተማሪዎች አገልግሎት ኃላፊዎች፣ የግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ኃላፊዎችና ሌሎች የሚመለከተቸው አካላት ሙስናን መከላከልና መቆጣጠርን አስመልክቶ ከታኅሣሥ 05 - 06/2016 ዓ/ም የሚቆይ የመጀመሪያ ዙር ሥልጠና በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እየሰጠ ይገኛል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ሚኒስቴር ሱፐርቪዥን ቡድን በተሰጠው ግብረ መልስና ሌሎች ተያያዥ ተቋማዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከመኅበረሰቡ ውይይት እያካሄደ ይገኛል
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ሚኒስቴር ሱፐርቪዥን ቡድን ለዩኒቨርሲቲው በሰጠው ግብረ መልስና ሌሎች ተያያዥ ተቋማዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ጋር ከታኅሣሥ 04-11/2016 ዓ/ም ድረስ በሁሉም ካምፓሶች ከአስተዳደር ሠራተኞችና መምህራን ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

- Details
በኢፌዲሪ ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አማካኝነት የስፓኒሽ ኤጀንሲ “Agency for International Development Cooperation/AECID” ለዩኒቨርሲቲው አዲስ ገቢ ሴት ተማሪዎች አገልግሎት የሚውሉ 16 ኮምፒውተሮች ከነወንበርና ጠረጴዛቸው፣ አንድ የቀለም ፕሪንተር፣ አንድ የፎቶኮፒ ማሽን፣ አንድ ፕሮጀክተር፣ ሦስት የዋይፋይ ራውተርና ሌሎች አጋዥ ግብዓቶችን ኅዳር 28/2016 ዓ/ም አበርክቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ ሴት ተማሪዎች አገልግሎት የሚውል የኮምፒውተር ድጋፍ ተበረከተ

- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ከባህልና ቋንቋ ጥናት ተቋምና ከምርምር ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር ‹‹Female Presence in Research and Grant writing›› በሚል ርእስ ለዩኒቨርሲቲው ሴት መምህራን በምርምርና ግራንት አጻጻፍ ዙሪያ ከታኅሣሥ 01-04/2016 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ