- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከቤልጂየም ሀገር 5 ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በትብብር የሚሠራው “AMU-IUC – Arba Minch University – Institutional University Cooperation” ፕሮግራም 2ኛ ዙር የኢፌዲሪ ሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ታገሠ ጫፎና በኢትዮጵያ የቤልጂየም አምባሳደር ስቴፋን ቲጂስ/Stefaan Thijis/ በተገኙበት መስከረም 11/2015 ዓ/ም በይፋ ተጀምሯል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
- Details
አቶ ሙሉነህ መንገሻ ከአባታቸው ከአቶ መንገሻ ቃንኤ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ዓለሚቱ በላቸው በቀድሞ በሰሜን ኦሞ ዞን በጋሞ አውራጃ በቁጫ ወረዳ መስከረም 12/1958 ዓ.ም ተወለዱ፡፡
የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በቀድሞ በጎፋ ወረዳ በገልጣ ከተማ 1ኛ- 6ኛ ክፍል በገሪማ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት፣ ከ7ኛ- 8ኛ ክፍል በአርባ ምንጭ ከተማ በኩልፎ ሙሉ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት እና ከ9ኛ- 10ኛ ክፍል የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒቲ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አጠናቀዋል፡፡
- Details
ወ/ሮ መርታን መርዕድ ከአባታቸው ከአቶ መርዕድ ዱለቻ እና ከእናታቸው ወ/ሮ አየለች ቡሩኮ በአርባ ምንጭ ከተማ ወዜ ቀበሌ ጳጉሜ 3/1978 ዓ.ም ተወለዱ፡፡
የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን (ከ1ኛ - 6ኛ) ክፍል በዓለም 1ኛ ደረጃ ት/ቤት፣ የ7ኛ እና 8ኛ ክፍል ትምህርታቸውን በኩራዝ መለስተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እንዲሁም የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጂንካ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ያጠናቀቁ ሲሆን በ1996 ዓ.ም ሚዛን ቴፒ ግብርና ኮሌጅ በመግባት በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ትምህርት በ1998 ዓ/ም በዲፕሎማ ተመርቀዋል፡፡
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ለሁሉም ካምፓሶች ለተመራቂ ተማሪዎች ወደ ሥራ ዓለም ሲገቡ ሊገጥሟቸው የሚችሉ የብልሹ አሠራር ችግሮችን የመከላከል ግንዛቤን ለማዳበር ከመስከረም 5-6/2015 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያና በ2ኛ ዲግሪ መርሃ ግብሮች በመደበኛ፣ በማታ፣ በክረምት፣ በሳምንት መጨረሻ እና በተከታታይና ርቀት መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ የ35ኛው ባች 2ኛ ዙር 1,200 ተማሪዎችን መስከረም 12/2015 ዓ/ም አስመርቋል፡፡ ከተመራቂዎቹ መካከል 84ቱ በሕክምና ዶክትሬት ዲግሪ የተመረቁ ሲሆን ከአጠቃላይ ምሩቃንም 387ቱ ሴቶች ናቸው፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ ዲግሪና በ2ኛ ዲግሪ መርሃ ግብር ያሠለጠናቸውን የ35ኛ ባች ተማሪዎች ለ2ኛ ጊዜ አስመረቀ